Welcome
Login / Register
Loading...

Most Popular Articles


 • Ethiopia: Erso Behonu Men Yadergalu Radio Program | FanaBC

  እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?

  ትምህርት ቤት ከተዋወኳት ባለቤቴ ጋር በይፋ በጋብቻ ከመተሳሰራችን በፊት ብዙ ጊዜ በአብሮነት አሳልፈናል ከዚያም በሁለታችንም ቤተሰቦች መልካም ፈቃድ በ1997 ዓ.ም. ጋብቻ ፈጸምን።

  ስራየ ሹፍርና ሲሆን ባለቤቴ ደግሞ የቤት እመቤት ናት፤ በትዳራችን ሁለት የ8 እና የ6 አመት ልጆች አፍርተናል፤ ከልጆቼ እና ባለቤቴ ጋር ጊዜ የማሳልፈው በበዓላትና አንዳንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ ይሁን እንጅ ኑሯችን ሰላም፣ ፍቅር እና መተሳሰብ የሞላበት ነበር።

  የዛሬ ሶስት አመት ሱዳን ሃገር ትኖር የነበረች የባለቤቴ እህት በእንግድነት ወደ ቤታችን መጣች፤ በወቅቱ በስራ ምክንያት እኔ ቤት አልነበርኩም፤ ከስራ ወደ ቤት በተመለስኩበት አጋጣሚ ግን የባለቤቴ ሁኔታ እንደቀድሞው አልነበረም እጅግ ተለዋወጠችብኝ።

  "አንተ ምኔ ነህ? ባለቤቴ ወይስ?" ብላ ያልጠበኩትን ነገር ተናገረችኝ፤ በሁኔታው ደነገጥኩ እህቷ ምን እንዳለቻትም አላውቅም። ከዚያም ኑሯችንን ለማሻሻል መስራትና ለልጆቻችን ቅርስ መተው እንዳለብኝ አስረድቻት ተግባባን እና ጥሩ ጊዜ አሳልፈን ወደ ስራየ ተመለስኩ።

  ይህ ከሆነ ከአንድ አመት በኋላም እህቷ በድጋሚ ወደ ቤታችን መጣች እኔም በአጋጣሚ ለስራ ወጣሁ፤ ለስራ ከወጣሁ በኋላ ስልክ በተደጋጋሚ ብደውልም አታነሳም ከቀናት በኋላ መታመሟ ተነግሮኝ ወደ ቤት በመመለስ ካሳከምኳት በኋላ ለስራ ተመልሸ ወጣሁ፤ እየተመላለስኩም አስታመምኳት። በወቅቱ ግን ከጭንቀት ውጭ ምንም በሽታ አልነበረባትም እኔም አረጋግችያት በድጋሚ ወደ ስራየ ተመለስኩ።

  ከቀናት በኋላም ተመልሸ አዲስ አመት በጥሩ ሁኔታ አብረን አክብረንና 15 ቀናት ቆይቼ ወደ ስራየ ሄድኩ፤ ከሳምንት በኋላ ግን ያልጠበኩትን ነገር ሰማሁ፤ ስልክ ተደውሎ ባለቤቴ ልጆቹንና ቤቱን ጥላ መሄዷ ተነገረኝና በጣም ደነገጥኩ፤ ወደ ልጆቼም ተመለስኩ።

  ልጆቼን ለቤተሰቦቼ ሰጥቼ ባለቤቴን ማፈላለግ ጀመርኩ ላገኛት ግን አልቻልኩም፤ ትሄዳለች ብዬ የምጠረጥረው ቦታ ሁሉ ፈለኳት አላገኘኋትም ቤተሰቦቿም ሊያግዙኝ ፈቃደኛ አልሆኑም። በመጨረሻም ልጆቼን ለቤተሰቦቸ ሰጥቼ ጉዳዩን ለፖሊስ አሳውቄ ወደ ስራየ ተመለስኩ።

  ቤተሰቦቼም ጫና ስለበዛባቸው ልጆቼን ከእነርሱ ጥቂት በእድሜ ከፍ ለምትል የአክስቴ ልጅ አደራ ሰጧት፤ እርሷም ከትምህርቷ ጎን ለጎን ልጆቼን የመንከባከቡን ሃላፊነት ተረከበች።

  ከጥቂት ጊዜ በኋላ ባለቤቴ ልጆቼ ጋር እየደወለች ናፍቃችሁኛል እንዳልመጣ ግን አባታችሁ ብር ከለከለኝ ማለት ጀመረች፤ በደወለችበት ስልክ መልሼ ስደውል ሱቅ መሆኑ ተነገረኝ፤ ባለቤቴም በተደጋጋሚ እንደዚህ ማድረጓን ቀጠለች።

  ጉዳዩን ለማጣራት ያደረኩት ጥረት ግን እርሷ የምትጠቀመው የተለያየ ስልክ እና ቦታ ስለሆነ ሊሳካልኝ አልቻለም፤ ልጆቼ መረዳት የሚችሉበት ዕድሜ ላይ አይደሉምና እንዴት ላስረዳቸው?

  ከባለቤቴም ጋር በግልፅ ስላላወራን ትመለሳለች ብየ ብዙ ብጠብቅም ጭራሽ ልጆቼ እንዲጠሉኝ እያደረገች ነው፤ ልጆቼም የእናትና አባት ፍቅር እያገኙ አይደለም፤ ሌላ ባገባ እኔ ብዙ ጊዜ ለስራ ስለምወጣ ልጆቼ በእንጀራ እናት እንዴት ይሆናሉ ብዬ እጨነቃለሁ።

  ባሉበት እንዳይኖሩ ደግሞ የእርሷ ድርጊት ያስፈራኛል፤ አዕምሯቸውን እንዳታበላሽብኝም እሰጋለሁ።

  የአክስቴ ልጅም በልጀነቷ ሃላፊነት መሸከሟ እየከበደኝና ሁኔታዋም እያሳዘነኝ ነው፤ ምን ባደርግ ይሻለኛል?

  እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?

  Read more »
 • Meseret Mebrate and #Nibret Gelawe make their relationship official.- FALSE NEWS

  መሰረት መብራቴ እና ንብረት ገላው ተጣመሩ የተባለው ወሬ ሀሰት ነው Ethiopian artist’s #Meseret Mebrate and #Nibret Gelawe make

  their relationship official.- FALSE NEWS

  አርቲስት መሠረት መብራቴ ጋር ደውልኩላት፤ ‹‹… በተዛመተው ሀሰተኛ ወሬ በጣም አዝኛለሁ፤ የሀሰት ወሬውን ሳያረጋግጡ የሚቀባበሉትም ይገርማል፡፡ እንዲህ ሀሰተኛ ወሬ

  እየወለዱ የሚያሰራጩ፤ የግለሰቦችን ሕይወት የሚበጠብጡ ልዑል እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው፡፡ … እኔ የራሴ ሕይወት አለኝ፡፡ … እንዲህ አይነት ልቦለድ ታሪክ ማራባት

  በባህላችንም ነውር፤ በእምነታችንም ኃጢአት ነው፡፡ … Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)ስለደወልክልኝ አመሰግናለሁ፡፡

  አርቲስት ንብረት ገላው፤ (እከ) ጋርም ደወልኩ፡፡ እንዲህም አለ፤ ‹‹ሠርጌን በፌስቡክ አይቼዋለሁ፡፡ የመልስ ጥሪ እየጠበኩኝ ነው፡፡ … ወሬው ሀሰት ነው!›› ብሏል

  ***

  በማኅበራዊ ድረ ገጽ የተናፈሰው እና በቅብብሎሽ የሄደው ወሬ እንዲህ ይላል

  የመሲና እከ ጉዳይ . . .

  ከአርቱ ባሻገር በቤተ ክርስቲያን አገልጋይነታቸው የሚታወቁት ሁለቱ ተዋንያን ለለፉት 3 አመታት በድብቅ ግንኙነታቸውን ይፋ ማድረግ ጀምረዋል:: ላለፉት ሳምንታት በዱባይ

  እና ታይላንድ የሽር ሽር ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት ጥንዶቹ ትላንት በአራራት ሆቴል የአትሌት ደራርቱ ቱሉ 25ኛ ዓመት የባርሴሎና ድልን

  በማስመልከት የተገኙት መሲና እከ በአደባባይ ፍቅሬ ብሎ ወደ መድረክ በመጥራት ጭምጭምታውን ይፋ አድርጎታል:: አትሌት ደራርቱ ቱሉም በመምጣታቸው ምስጋና

  ካቀረበች በኋላ ‹‹ለሠርጋችሁ ያብቃን ስትል መርቃቸዋለች›› መሉ ቪዲዮውን እሁድ በJTV ልዩ ልዩ ፕሮግራም ላይ ይቀርባል::

  የሀበሻ ቆንጆ

  ምንጭ፡ ከ ጌጡ ተመስገን የፌስ ቡክ ገፅ

  Read more »
 • Ethiopia: መቐለ ከተማ 3 አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

   

  መቐለ ከተማ 3 አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

  መቐለ ከተማ በክረምቱ የሚያደርገውን የዝውውር እንቅስቃሴ በማጠናከር ሶስት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ ሙሉጌታ ረጋሳ ፣ አለምነህ ግርማ እና ዮሴፍ ድንገቱ ለመቐለ የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

  የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዮሴፍ ድንገቱ በወላይታ ድቻ 6 የውድድር ዘመናትን ማሳለፍ የቻለ ተጫዋች ሲሆን ክለቡ ከብሔራዊ ሊግ ጀምሮ ባሉት አመታት ባደረገው ጉዞ ከሚጠቀሱ ቁልፍ ተጫዋቾች አንዱ ነበር፡፡

   

  የግራ መስመር ተከላካይ የሆነው አለምነህ ግርማ በ2007 ክረምት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ኢትየዮ ኤሌክትሪክን ከተቀላቀለ በኋላ ወጣ ገባ በሆነ ሁኔታ የመሰለፍ እድል አግኝቷል፡፡

  ሌላው ለክለቡ የፈረመው የመስመር አጥቂው ሙሉጌታ ረጋሳ ነው፡፡ ወልዲያ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ አስተዋፅኦ ካደረጉ ተጫዋቾች መሀል የሚጠቀስ ተጫዋች ነው፡፡

   

  መቐለ ከተማ በዝውውር መስኮቱ በስፋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን እስካሁንም ሶስቱን ተጫዋቾች ጨምሮ 10 አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ቀላቅሏል፡፡

  spurce: soccoerEthiopia.net

  Read more »
RSS